Thursday, 23 October 2014

ሃብታሙ አያሌው በጠና ታሟል – ሆስፒታል ነው ዛሬ የዋለው

ሚሊየኖች ድምጽ) የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና የሚሊዮኖች ግብረ ኃይል ሰብሳቢ የነበሩት፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው በጸና መታመማቸዉንና ዛሬ በሆስፒታል መዋላቸዉን ለማረጋገጥ ችለናል።
habtamu ayalew
የማእከላዊ እሥር ቤት ብዙ ቶርቸር የሚደረግበት እስር ቤት እንደሆነ ይታወቃል። አቶ ሃብታሙ አያሌው ከብሎገር አብርሃ ደሳታ፣ ዳን ኤል ሺበሺና የዚዋስ አሰፋ ጋር ሐመሌ 1 ቀን የታሰሩ ሲሆን፣ ፖሊስ «መረጃ ለማሰባሰብ ጊዜ ይሰጠኝ» በሚል አራት ጊዜ ለሃያ ስምንት ፣ ሃያ ስምንት ቀናት መጠየቁ መዘገቡ ይታወሳል። በፍርድ ቤቱ የተቀመጡ ዳኞችም፣ ፖሊሲ ምንም አይነት መረጃ ሳያቀርብ፣ የእነ ሃብታሙን የዋስትና መብት በመከልከልና በወህኒ እንዲቆዩ በመፍቀድ፣ ሕግን የሚያስፈጽሙ ሳይሆን ፣ ለሕጉ ዉጭ በቀጥታ የፖሊስን መመሪያ የሚይሳተናግዱ መሆናቸዉን አሳይተዋል።
አቶ ሃብታሙ በአገራችን ፖለቲክ ትግል በዘመናችን የተነሱ አንጋፋ ፖለቲከኛ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ገዢው ፓርቲ በርሳቸው ላይ ኢሰብአዎና ኢፍትሃዊ ግፍ መፈጸሙ በካላላቸው ላይ ጉዳይና ሕመም ቢያስከትለም፣ በመንፈሳቸው ግን ከመቼዉም ጊዜ በላይ ጠንካራ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል።
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35627#sthash.65J25wuG.dpuf

Wednesday, 22 October 2014

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ወገንተኝነቱን የሚያሳይበት ወቅት አሁን ነው!

ዘረኛውና ፋሽስታዊው የህወሓት አገዛዝ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝነት በመከፋፈል ሹመቱና ጥቅማ ጥቅሙን ለራሱ ወገን፣ ችግሩንና መከራዉን ግን ለሌላው ኢትዮጵያዊ ያደለ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ሳይማሩና ሳይሰለጥኑ የጄኔራልነት ማዕረጎችን በሙሉ ሰብስበው የወሰዱት የህወሓት አባላት መሆናቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው።
በወያኔ መዳፍ ውስጥ እየተሰቃየች ባለችው ኢትዮጵያችን ውስጥ በዘርም ይሁን በፓለቲካ አመለካከት ከህወሓት የተለዩ ኢትዮጵያዊያን ቢማሩም ቢሰለጥኑም ለከፍተኛ አመራርነት እንደማይበቁ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያየነው ነው። አገዛዙ ቅራኔ ውስጥ በገባባቸው ቦታ ሁሉ እየዘመቱ ሕይወታቸውን እየገበሩ ያሉት ግን በመካከለኛና ዝቅተኛ ማዕረጎች ያሉ ኢትዮጵያዊያን መኮንኖችና ብዙሃኑ የሠራዊቱ አባላት የሆኑ ወታደሮችናቸው። ብዙሃኑ የሠራዊት ክፍል አለቆቹን ከመጠበቅ ባለፈ ድምጹን ከፍ አድርጎ ለመናገር እንኳን የማይፈቀድለት ሎሌ ተደርጓል።
ለኢትዮጵያዊ ወታደር ለህወሓት ሎሌ ከመሆን በላይ የሞት ሞት የለም። ብዙሃኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊቱ አባላት በጥቂት የወያኔ ሹማምንት የሚረገጥ መሆኑ የሠራዊቱን አባላት የግል ስብዕና ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሠራዊቱን ክብር ይነካል። የሠራዊታችን የህወሓት አገልጋይ መሆን የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያን ያዋርዳል። ይህ ዉርደት በዚህ ሁኔታ መቀጠል የለበትም።
ከእንግዲህ ጄኔራሎችና ሌሎችም የበላይ አዛዦች ሁሉ የአንድ አካባቢ ተወላጆች በሆኑበት ሠራዊት ውስጥ ተስማምቶ መኖር መቀጠል እያንዳንዱን የመከላከያ ሠራዊት አባል ሊያሰፍር ይገባል። የህወሓት ጄኔራሎች ጮማ በውስኪ ሲያወራርዱ፤ በህንፃዎች ግንባታ፣ በባንኮች ንግድ፣ በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተሰማርተው ቢዝነሳቸውን ሲያጧጥፉ፣ ምስኪኖቹ የሠራዊቱ አባላት በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአማራና በሌሎች የአገሪቱ ግዛቶች እየተወረወሩ ወገኖቻቸውን የሚፈጁበት ሥርዓት ማብቃት አለበት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ብዙሃኑ አባላት ቤተሰቦቻቸው በችጋር እየተቆሉ የአዛዦቻቸው ሀብት ጠባቂ መሆናቸው ማክተም አለበት።
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የጭለማ ዘመን ታሪክ እያበቃ መሆኑን የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ነው። መሣሪያዎቻቸውን እንደያዙ የነፃነት ኃይሎችን የሚቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨረመ መጥቷል። ሠራዊቱ ከሕዝብ ጎን እንደሚቆም ውስጥ ውስጡን የሚላኩ መልዕክቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። ይህ አበረታች ዜና ነው፤ ግን በቂ አይደለም። ወያኔን ከውስጥም ከውጭም የምናጣድፍበት ጊዜው አሁን ነው። የነፃነት ኃይሎችን መቀላቀያ ጊዜ አሁን ነው፤ በሠራዊቱ ውስጥም በህቡዕ መደራጃ ጊዜ አሁን ነው። ይህን ጊዜ መጠቀም ብልህነት ነው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ጥቂት የህወሓት ጥጋበኞች በብዙሃኑ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ላይ የሚያደርሱት በደል ማብቃት አለበት ይላል። ግንቦት 7፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሙስና የደለቡት፣ ትዕቢተኛና ጨካኝ መሪዎቻቸው ፍጹም ኢትዮጵያዊ ባህርይ የሌላቸው ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች እንደሆኑ በመረዳት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ክንዱን እንዲያነሳባቸው ጥሪ ያደርጋል። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሕዝብም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አንድ ወጥ እንዳልሆነ እና በመካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ ያሉ መኮንኖችና አብዛኞዎቹ ወታደሮች የሕዝብ ወገን መሆናቸውን እንዲገነዘብ ያሳስባል። “አብረን ነው ዘረኛውና ፋሽስቱን ወያኔን ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ አውርደን የምንጥለው” ስንል አብዛኛው የመከላከያ ሠራዊታችን ኢትዮጵያዊ ወገናችን እንደሆነ እና በወደፊቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ውስጥም ጉልህ ሚና እንዲጫወት የምንፈልግ መሆኑን ግልጽ ማድረግ እንሻለን። የመከላከያ ሠራዊቱም የሕዝብ ወገንተኝነቱ በተግባር እንዲያሳይ ጥሪ እናደርጋለን። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ አካል ነው፤ የሕዝብ ወገናዊነቱ በተግባር የሚያሳይበት ትክክለኛ ጊዜ ደግሞ አሁን ነው እንላለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አደረጉ

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አደረጉ

OLYMPUS DIGITAL CAMERA
ቅዳሜ ጁለይ 12/2014 በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አዘጋጅነት ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን በሚል አላማ በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የደንነት ሀይሎች መታፈንና ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ታላልፈው መሰጠታቸውን በተመለከተ ወደ ፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከተለያዩ ከተሞች በመሰባሰብ በኖርዌ ኦስሎ ለአምስት ሰዓታት የፈጀ ውይይት ሲያደርጉ ውለዋል::
ሕዝባዊ ውይይቱ ከቀኑ 15: 00 ሰአት ላይ የተጀመረ ሲሆን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያኖች የአቶ እንዳርጋቸው ምስል ያለበትና ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን የሚል ጹሁፍ የተጻፉበትን ቲሸርት በመልበስ ለስብሰባው ድምቀት የሰጡት ሲሆን ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውንም የትግል አጋርነት አስማስክራዋል እነዚህን ቲሸርቶች የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርንጫፍ በራሳቸው አነሳሽነት የሰሩ ሲሆን የድጋፍ ድርጅታችን ወጪውን በመሸፈን ለተሰብሳቢው በነጻ ኣድሏል።
ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት አላፊ አቶ አቢ አማራ በሃያ ሶስት አመታት በወያኔ ጨካኝ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉትና በግፍ ለሚሰቃይዩ ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማስደረግ አስጀምረውታል በመቀጠልም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር በስብሰባው ላይ የተገኛውን ሕዝብ እንኮን ደህና መጣችሁ በማለትና በማመስገን ፐሮግራሙን በንግግር የከፈቱት ሲሆን አቶ ዮሀንስ በንግግራቸው የወያኔ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ባደረሰው አፈና ግንቦት 7 የክተት አዋጅ ማስተላለፉን ጠቅሰው አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በአሁን ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል እየታገሉ ባሉ ታጋዮች ላይ ሳይቀር እስር እያደረሰባቸው እንዳለ በማመልከት ሰሞንኑን እንኮን የሰመያዊ፣ የአንድነት፣ የአራና የፖለቲካ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ለስር ተዳርገዋል ብለዋል::
OLYMPUS DIGITAL CAMERAOLYMPUS DIGITAL CAMERA
ስለሆነም ህዝባችንን ለእስር እያደረገ ያለውን አገዛዝ ለመቃወም ሁሉም በአንድነት መሰባሰብ እንዳለበት አጠንክረው በመናገር በአሁን ሰአት የአቶ አንዳርጋቸው በወያኔ መታፈንና መታሰር መላውን ኢትዮጵያ ዳር እስከ ዳር እያንቀሳቀሰውና ሕዝቡም እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በማለት በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጠቅሰው በአሁን ሰአት ትግሉ የግንቦት 7 ብቻ አይደለም ይህን ትግል በዚሁ አንድ ሆነን መቀጠል እለብን ብለዋል::
በመቀጠል አቶ ደባስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባል የአቶ አንዳርጋቸውን ከወጣት እድሜያቸው ጀምሮ ያለውን የፖለቲካ አካሄድ አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ማን ነው ? በሚል ርእስ የአቶ አንዳርጋቸውን የትግል ጉዞ የሚዳስስ ዘገባ ሰፋ ባለ ትንታኔ በጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በስብሰባው ላይ የኢሀፓ ፣ የአርበኞች ግንባር፣ የሸንጎ ፣የስደተኛው ማህበር ተወካዮች እና ሌሎችም ሰዎች በየተራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የየድርጅቷቹም ተወካዮች የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መታፈንና ለእስር መዳረግን በተመለከተ የድርጅታቸውን አቋም ለተሰብሳቤው ያስረዱ ሲሆን የሁሉም ፖርቲ ተወካይች በአቶ አንዳርጋቸው መታፈንና ለእስር መደረግ ማዘናቸውን ገልጸው ሁሉም በአንድነት በመተባበር በማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ የወያኔንን መንግስት ማስወገድ እንዳለባቸው አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል::
በየፕሮግራሞቹ መሀል ግጥሞችና ሌሏችም ፕሮግራሞች ቀርበው የመጀመሪያው ዞር ተጠናቋል::ከ30 ደቂቃ የእረፍት የሻይ እና የቡና ፕሮግራም በኋላ የሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ፕሮግራም በተያዘለት ጊዜ ተጀምሮ የፕሮግራሙን ተሳታፊዎች ያሰተፈ ፕሮግራም በአቶ አብዱ የሱፍ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ስታቫንገር ቅርንጫፍ ምክትል ሊቀመንበር ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና ተግባሪዊ የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪን ካብራሩ በኋላ ለተሰብሳቢው ለውይይት በማቅረብ በኖርዌ የምንኖር ኢትዮጵያኖች ይህን የትግል ጥሪ ለማስፈጸም ምን እናድርግ በማለት ለውይይት አቅርበው የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በአቶ ዮሀንስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር አወያይ አማካኝነት በስፋት ተወያይተውበታል ::
ተሰብሳቢውም በብዙ ነገሮች ከተወያዩ በኋላ ይሄ ግንቦት 7 ያወጣውን የመጀመሪያ እንከን የትግል ጥሪ ተግባራዊ በየቦታው አለም አቀፍ ታክስ ፎርሶች እየተቋቋሙ እንዳለና በኖርዌይም ይህንኑ ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቷች ያካተተ ታክስ ፎርስ እንዲቋቋም ተወስኖል:: በመቀጠልም በተሰብሰቢዎች በተመረጡ ሰዎች የተጻፋ ባለ ስድስት አሃዝ የተሰብሳቢው የአቋም መግለጫ ለጉባሄው በጹሁፍ ቀረቦል:: ተሰብሳቢው ያወጣው የአቋም መግለጫ
1. ሁላችንም አንዳርጋቸው ወይም አንድ አርጊያቸው ነን ስንል ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሐገራችን ኢትዮጵያ ለማስፈን የሚከፈለውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ማለታችን ነው።
2. የተለያዩ የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት የሚያደርጉትን መጠላለፍ እንዲቀርና በጋራ ወይም አንድ በመሆን እንዲሰሩ ግፊት እናደርጋለን።
3. ለሚቀርብልን ሐገርን የማዳን ጥሪ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።
4. የየመን መንግስት ከአለም አቀፍ ህግ ጋራ የሚፃረር ስራ በመስራት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለወያኔ አሳልፎ በመስጠት የሰራውን ወንጀል ለዓለም አቀፍ ህግ የማቅረብ ስራ በጋራ እንደምንሰራ።
5. የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ መታፈን ትግሉን የበለጠ እንደሚያጠናክረውና ወደ ውጤት እንዲያመራ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናደርጋለን።
6. ወያኔ የተለያየ ምክንያት በመፍጠር ኢትዮጵያውያንን እስርቤት ማስገባቱን እንዲቀርና የታሰሩትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ እንጠይቃለን በማለት የአቋም መግለጫ አውጥተዋል ።
በመጨረሻም አቶ ዳንሄል አበበ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ምክትል ሰብሳቢ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የአቋም መግለጫ ለተሰብሳቢው በጹሁፍ ያሰሙ ሲሆን በንግግራቸውም አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የቋሙ የነጻነት ታጋይ ናቸው እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ የምንል ሁሉ ለሃያ ሶስት አመታት ህዝብን በዘረኝነት የከፋፈለውን ወያኔን በቃ ልንለው ይገባል ካሉ በኋላ በኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ አፈና፣ ግድያው፣ እስራቱ መጨመሩን በመናገር ይኼን ጨቋኝና አፋኝ ስርአት ለማስወገድ እንነሳ በማለት ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን በመጨረሻ እኔ እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ እናንተስ በማለት የፕሮግራሙን ተሳታፊ በመጠየቅ ፕሮግራሙ በተያዘለት ሰዓት ከምሽቱ 20:00 ተጠናቋል ::
እኛ ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ

በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች በእልህና በቁጣ የተሞላ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች በእልህና በቁጣ የተሞላ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

10465232_418561384950271_4183653452522972315_o
ሰኞ ጁላይ 14, 2014 የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ አዘጋጅነት በኖርዌ ኦስሎ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያኖች በአንድ ላይ በመሰብሰብ ከቀኑ 13፡00 ጀምሮ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ በየመን የፀጥታ ኃይሎች ታፍነው በአምባገነኑ ወያኔ እስር ቤት መታሰራቸውን በመቃወም እና በተጨማሪም አቶ ኦኬሎ አኳይ የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውና በኖርዌ ሃገር ይኖሩ የነበሩ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት ከሱዳን በወያኔ የደህንነት ኃይሎች በግፍ ታፍነው መወሰዳቸውንና በወያኔ እስርቤት ታስረው ለሞት ፍርድ መዳረጋቸውን በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።ሰልፈኞቹ መነሻቸውን በኖርዌጅያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረጉ ሲሆን በዛው በኖርዌጅያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በመገኘት የወያኔን ህገወጥ አፈና እና እስራት የሚቃወሙ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝና በማሰማት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። በስፍራው የነበሩ ሰልፈኞቹ ሲያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል በጥቂቱ ኦኬሎ አኳዮ ይፈታ፣ ኖርዌይ ዜጋሽ ኦኬሎ አኳዮ የት ነው ያለው?፣ ኦኬሎ አኳዮ አሸባሪ አይደለም የሚሉ የተለያዩ መፈክሮች ይገኙበታል ::በማያያዝም ሰልፈኞቹ የኖርዌ መንግስት ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት የምትሰጠውን እርዳታ እንድታቆምም ጠይቀዋል:: በእለቱ የተዘጋጀውን ደብዳቤ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አማካኝነት ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ አስረክበዋል። ተወካይዋም ደብዳቤውን ከተቀበሉ በኋላ ጉዳዩ ን እንደሚያዩትና ችግሩ አሳሳቢ ከመሆኑም አኳያ በትኩረት እየተከታተሉት እንደሆነ አሣውቀዋል። 10513325_418562201616856_7326119886570834522_n
10507128_418560668283676_4408161006652666291_o  10275451_418561521616924_1229527644438567622_oበመቀጠልም ሰልፈኞቹ በቀጥታ ጉዟቸውን ወደ እንግሊዝ ኢምባሲ በማቅናት ታላቅ እልህና ቁጣ የተቀላቀለበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን በዛው በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመሆን የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ጩህትና በስሜት ሲያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል Britin were is you citizen, Free Andrgachew Tsige, where is your action, stop discrimination among citizens, we are all Andrgachew Tsige, Brtain dont support terrirost regim in Ethiopia የሚሉት ይገኙበታል:: እነዚሁ በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያ ሰልፈኞች በዚሁ በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ባለፈው ጁላይ 3, 2014 ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወሳል::የዛሬው ሰልፍ ከባለፈው ሰልፍ እጅግ በጣም ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ሰልፈኞቹ በጠቅላላ እኔም አንዳርጋቸው ፅጌ ነኝ የሚል የአንዳርጋቸውን ምስል የያዘ ቲሸርት የለበሱ ሲሆን ለሰልፉም ድምቀትን በመስጠት ለነጻነት ታጋዩ ለአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ያላችውን ፍቅር በአደባባይ ያስመሰከሩ ሲሆን የተቃውሙ ሰልፉም በሰልፈኞቹ ቁጣና እልህ የተሞላበት እንደነበር ለማየት ተችሏል::ሰልፈኞቹም የያዙትን ደብዳቤ በሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ ተወካይ በአቶ ዳዊት መኮንን በኩል ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ ያስረከቡ ሲሆነ ተወካይዋም ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው፣ በትኩረትና በቅርበት እየሰሩ መሆኑን እንዲሁም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ነፃ እስኪወጡ ድረስ የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉና ክትትላቸውን እንደሚቀጥሉ ለሰልፈኛው አሳውቀዋል። በመጨረሻም ሰልፈኞቹ በአንድ ላይ በመሆን የግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል መዝሙር ላንቺ ነው ሐገሬ ላንቺ ነው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው የሚለውን ህዝባዊ መዝሙር በደማቅና በሀገራዊ ስሜት ዘምረው ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ ከቀኑ 15፡00 ተጠናቋል።
ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

አቶ ቴዎድሮስ አድሐኖም በኖርዌይ ኦስሎ ተዋረደ

አቶ ቴዎድሮስ አድሐኖም በኖርዌይ ኦስሎ ተዋረደ

በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ invest in Ethiopia በመሚል ሽፋን የኖርዌጅያን አፍሪካን የንግድ ማህበር ባዘጋጀው የኖርዌይ ባለሃብቶች ስብሰባ ላይ ለመካፈል በእለቱ ከቀኑ 08፡35 ወደ ኦስሎ የመጣው የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም በኖርዌይ በሚኖሩና ከተለያዩ ከተሞች በመጡ ቁጥራቸዉ ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ውግዘትና ዉርደት ያጋጠመው ሲሆን፥ ስብሰባው ካለቀም በኋላ ወዳረፈበት የግራንድ ሆቴል በአምስት የፖሊስ መኪና ታጅቦ ለመግባት ሲሞክር መረጃውም ቀድሞ በመድረሱና ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩት ኢትዮጵያውያን በመጣበት መኪና ላይ የእንቁላል ናዳ በማውረድ ለረጅም ሰአታት ከመኪናው እንዳይወጣ ያረጉት ሲሆን፥ በስፍራውም ቀደም ብሎ የተሰማራው በርካታ ልዩ የፀጥታ ሃይል ድርጊቱ ለማስቆም ቢሞክርም አልበገር ያሉት ኢትዮጵያውያኖች ቁጣቸውን አሳይተዋል፥፥ ጉዳዩን የኖርዌይ ትልቁ የመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ NRK በሰበር ዜናዉ የዘገበው ሲሆን በሰውዬው ላይ እንቁላል መወርወሩንና ተቃሞውም በልዩ ፀጥታ ሃይል መብረዱን ዘግበዋል፥፥
ከመጀመሪያውም ፍርሃት ያደረባቸው ወያኔዎች ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግላቸው በጠየቁት መሰረት ከፍተኛ ጥበቃ የነበረ ሲሆን የህዝቡ ቁጣም ከበረደ በኋላ ወዳረፈበት ሶስተኛ ፎቅ ሲያመራ ሆቴል ዉስጥ የሚጠባበቁ የቁርጥ ቀን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በልዩ የፀጥታ ሃይሎች ተገደው ሊወጡ ችለዋል፥፥ በተጨማሪም አመሻሹ ላይ እዛው በሆቴሉ ውስጥ ለስብሰባ ሊደረግ ታስቦ የነበረ ሲሆን በቦታው የተገኙት ቁጥራቸው 15 የሚሆኑ የስርአቱ አገልጋዮች ተገኝተው የነበረ ሲሆን አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናዶ እንደነበርና ይህ ዓይነት ተቃውሞ ባለበት ሁኔታ ስብሰባ ማድረግ እንደማይችል በመናገሩ ስብሰባው ተቀይሮ የሻይ ምሽት አርገው መለያየታቸውን ከስፍራው የደረሰን ሚስጥራዊ መረጃ ያመለክታል፥፥
በዚህ አጋጣሚም በኖርዌይ ውስጥ የሚሰራጨው በወያኔ መንግስት በጀት የሚተዳደረው የወያኔ ልሳን www.abesha.no ድህረ ገጽ እንደተለመደው ኢትዮጵያውያኖች አያውቁም፥ አይሰሙም አያመዛዝኑም በሚል መንፈስ የተለያየ የማወናበጃና ያረጀበት የፕሮፖጋንዳ ጽሁፎችን ለማውጣት ቢሞክርም እንዲሁም በኖርዌይና በመላው አለም የሚኖሩ የወያኔን ወንጀል በማውጣት ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እንደተለመደው ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ከአሸባሪነት ጋር በማያያዝ ለማጣላት ባዶ ጭንቅላቱን ለመጠቀም የሞከረው የተለመድ የውሸት ዲስኩር አልተሳካም፥፥
በቀጣይነትም ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንቀርባለን፥፥

Tuesday, 7 October 2014

መስዋትነት ...

ዛሬ ወያኔ የሥልጣን ዘመኑ በጨመረ ቁጥር የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትህ ነፃነትና የዲሞክራሲ መብቱን እያጣ እንዲሁም የሚደርሰበት መከራ እየጨመረ መምጣቱ የማን አለብኝነትና የመኖር ዕድሜውን እያራዘመ እንደሆነ ማሳየቱን ቀጥሎአል።
ይህ ተግባሮት በቅርቡ በአቶ አንድአርጋቸዉ ፅጌ በሃገራችን በኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ ነፃነትና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ጊዜውን እዉቀቱንና ጉልበቱን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀና ዝግጅቱንም በዕዉን ያሳየ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ እንኳን ያልበቃቸዉ ዛሬም ድረስ የስለላቸዉን መረብ እየዘረጉ ከጋሻጃግሬዎቻቸዉ ጋር በማበር ኢትዮጵያውያንን ከየቦታው እያሳደዱ በማሰርና በማሰቃየት ይገኛሉ።
እነርሱም አሁንም ቂመኞች ናቸው፤ እነርሱ አሁንም ዘረኞች ናቸው፤ እነርሱ አሁንም የዘር ፖለቲካ እየረጩ ነው፤ እነርሱ አሁንም ለህዝቡ ለፍቅርና ለይቅርታ ምላሻቸዉ ትዕቢትና እቢሪት ጥላቻና እልህ፣ ቂምና ክፋት እየሆነ ነው። ይህም አልበቃ ብሎአቸዉ እንደፈረስ እየጋለቡ በወጣቱ ትውልድ ላይ ዘመቻቸውን እንደቀጠሉ ይገኛሉ።
ታድያ ይህ በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ኢሰባዊነት እጅግ አሳዛኝና ዘግናኝ በመሆኑ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን በተለያየ ቦታና ጊዜ እረፍት እየነሳዉ በቁጭት ላይ ይገኛል። በመሆኑም በሃገራችንና በወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው በደል አብቅቶ ያንን የምንናፍቀው ነፃነትና ፍትህ እንድንቀንናጅ ትግላችንን ማጠናከሩ አሁን ላይ አማራጭ የሌለዉና እጅ ለእጅ ተያየዘን፣ ተደጋግፈን የአምባገነኑን ወያኔ እድሜ ማሣጠር የምንችልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ሁላችንም የየበኩላችንን አስተዋዕፆ የምናሳይበት ሰዓት አሁን ነው።
አርበኛችንና የቁርጥ ቀን የሆነው ልጃችን አንዳርጋቸው እንዲሁም መሠል ኢትዮጵያዊያንን ወገኖቻችን በጨካኙ መሪ እጅ ስር መውደቃቸው አንገታችንን የሚያስደፋና ተስፋ የሚያስቆርጠን ሳይሆን እንደውም ከምንግዜውም በላይ የትግላችን ስልት ቀይሮና አጠናክሮት ይገኛል ።
በመሆኑም የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህን በሃገርና በህዝብ እየደረሰ ያለውን በደልና ግፍ ለመታገልና ጨርሶ ከስሩ ለመገርሰስ ለትግሉ የሚጠይቀዉን ሁሉ መስዋትነት እየከፈለ ይገኛል።
በዚህም መሰረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኦገስት 31,2014 ባዘጋጀው ወቅታዊ ስብሰባና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ በመካፈል ለሀገራችን ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ነፃነት ፍትህ ያስፈልጋታል የምንል ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በተመሳሳይም በኦስሎ በሚዘጋጀው ዝግጅት ላይ ተገኝተን ሃገራዊ ጥሪ አጋርነታችንንና ግዴታችንን መወጣት አለብን እላለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኖራለች!!!