አቶ ቴዎድሮስ አድሐኖም በኖርዌይ ኦስሎ ተዋረደ
በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ invest in Ethiopia በመሚል ሽፋን የኖርዌጅያን አፍሪካን የንግድ ማህበር ባዘጋጀው የኖርዌይ ባለሃብቶች ስብሰባ ላይ ለመካፈል በእለቱ ከቀኑ 08፡35 ወደ ኦስሎ የመጣው የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም በኖርዌይ በሚኖሩና ከተለያዩ ከተሞች በመጡ ቁጥራቸዉ ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ውግዘትና ዉርደት ያጋጠመው ሲሆን፥ ስብሰባው ካለቀም በኋላ ወዳረፈበት የግራንድ ሆቴል በአምስት የፖሊስ መኪና ታጅቦ ለመግባት ሲሞክር መረጃውም ቀድሞ በመድረሱና ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩት ኢትዮጵያውያን በመጣበት መኪና ላይ የእንቁላል ናዳ በማውረድ ለረጅም ሰአታት ከመኪናው እንዳይወጣ ያረጉት ሲሆን፥ በስፍራውም ቀደም ብሎ የተሰማራው በርካታ ልዩ የፀጥታ ሃይል ድርጊቱ ለማስቆም ቢሞክርም አልበገር ያሉት ኢትዮጵያውያኖች ቁጣቸውን አሳይተዋል፥፥ ጉዳዩን የኖርዌይ ትልቁ የመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ NRK በሰበር ዜናዉ የዘገበው ሲሆን በሰውዬው ላይ እንቁላል መወርወሩንና ተቃሞውም በልዩ ፀጥታ ሃይል መብረዱን ዘግበዋል፥፥
ከመጀመሪያውም ፍርሃት ያደረባቸው ወያኔዎች ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግላቸው በጠየቁት መሰረት ከፍተኛ ጥበቃ የነበረ ሲሆን የህዝቡ ቁጣም ከበረደ በኋላ ወዳረፈበት ሶስተኛ ፎቅ ሲያመራ ሆቴል ዉስጥ የሚጠባበቁ የቁርጥ ቀን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በልዩ የፀጥታ ሃይሎች ተገደው ሊወጡ ችለዋል፥፥ በተጨማሪም አመሻሹ ላይ እዛው በሆቴሉ ውስጥ ለስብሰባ ሊደረግ ታስቦ የነበረ ሲሆን በቦታው የተገኙት ቁጥራቸው 15 የሚሆኑ የስርአቱ አገልጋዮች ተገኝተው የነበረ ሲሆን አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናዶ እንደነበርና ይህ ዓይነት ተቃውሞ ባለበት ሁኔታ ስብሰባ ማድረግ እንደማይችል በመናገሩ ስብሰባው ተቀይሮ የሻይ ምሽት አርገው መለያየታቸውን ከስፍራው የደረሰን ሚስጥራዊ መረጃ ያመለክታል፥፥
በዚህ አጋጣሚም በኖርዌይ ውስጥ የሚሰራጨው በወያኔ መንግስት በጀት የሚተዳደረው የወያኔ ልሳን www.abesha.no ድህረ ገጽ እንደተለመደው ኢትዮጵያውያኖች አያውቁም፥ አይሰሙም አያመዛዝኑም በሚል መንፈስ የተለያየ የማወናበጃና ያረጀበት የፕሮፖጋንዳ ጽሁፎችን ለማውጣት ቢሞክርም እንዲሁም በኖርዌይና በመላው አለም የሚኖሩ የወያኔን ወንጀል በማውጣት ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እንደተለመደው ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ከአሸባሪነት ጋር በማያያዝ ለማጣላት ባዶ ጭንቅላቱን ለመጠቀም የሞከረው የተለመድ የውሸት ዲስኩር አልተሳካም፥፥

በቀጣይነትም ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንቀርባለን፥፥
No comments:
Post a Comment