በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች በእልህና በቁጣ የተሞላ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ
ሰኞ ጁላይ 14, 2014 የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ አዘጋጅነት በኖርዌ ኦስሎ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያኖች በአንድ ላይ በመሰብሰብ ከቀኑ 13፡00 ጀምሮ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ በየመን የፀጥታ ኃይሎች ታፍነው በአምባገነኑ ወያኔ እስር ቤት መታሰራቸውን በመቃወም እና በተጨማሪም አቶ ኦኬሎ አኳይ የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውና በኖርዌ ሃገር ይኖሩ የነበሩ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት ከሱዳን በወያኔ የደህንነት ኃይሎች በግፍ ታፍነው መወሰዳቸውንና በወያኔ እስርቤት ታስረው ለሞት ፍርድ መዳረጋቸውን በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።ሰልፈኞቹ መነሻቸውን በኖርዌጅያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረጉ ሲሆን በዛው በኖርዌጅያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በመገኘት የወያኔን ህገወጥ አፈና እና እስራት የሚቃወሙ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝና በማሰማት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። በስፍራው የነበሩ ሰልፈኞቹ ሲያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል በጥቂቱ ኦኬሎ አኳዮ ይፈታ፣ ኖርዌይ ዜጋሽ ኦኬሎ አኳዮ የት ነው ያለው?፣ ኦኬሎ አኳዮ አሸባሪ አይደለም የሚሉ የተለያዩ መፈክሮች ይገኙበታል ::በማያያዝም ሰልፈኞቹ የኖርዌ መንግስት ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት የምትሰጠውን እርዳታ እንድታቆምም ጠይቀዋል:: በእለቱ የተዘጋጀውን ደብዳቤ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አማካኝነት ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ አስረክበዋል። ተወካይዋም ደብዳቤውን ከተቀበሉ በኋላ ጉዳዩ ን እንደሚያዩትና ችግሩ አሳሳቢ ከመሆኑም አኳያ በትኩረት እየተከታተሉት እንደሆነ አሣውቀዋል። 



ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
No comments:
Post a Comment